የ COVID-19 በኪራይ ላይ የሚሰጥ ድጋፍ አለ

የኪራይ መክፈያ ጊዜዎ ካለፈ ወይም ከኪራይ ቤት የመባረር አደጋ ላይ ከሆኑ፣ ሶስት አማራጮች አሉዎት።

  • የኪራይ ድጋፍ። በመላ አገሪቱ የሚገኙ የአከባቢ ድርጅቶች የቤት ኪራይ ድጋፍን በማቅረብ ላይ ናቸው። እርስዎ ወይም አከራይዎ እንዴት ማመልከት እንደሚችሉ መረጃ ለማግኘት በካውንቲዎ ውስጥ ያለውን የአከባቢውን ድርጅት ማነጋገር ይችላሉ።

    የኪራይ ድጋፍ አቅራቢዎች ዝርዝር፦ https://www.commerce.wa.gov/serving- communities/homelessness/eviction-rent-assistance-program/

    ዕድሜዎ ከ 25 ዓመት በታች ከሆነ ተከራይ ከሆኑ ፣ የአከባቢውን የ የወጣቶች እና የወጣት ጎልማሶች ከቤት ማስወጣት የኪራይ እርዳታ መርሃ ግብር አቅራቢን ያነጋግሩ። ዝርዝር፦ https://www.commerce.wa.gov/serving-communities/homelessness/youth- and-young-adult-eviction-rent-assistance-program/

  • ከቤት የማስወጣት የመፍትሄ መርሃ ግብር። እርስዎ ወይም አከራይዎ በሚኖሩበት ካውንቲ ውስጥ በአከባቢዎ ያለውን የግጭት መፍቻ ማዕከልን ማነጋገር ይችላሉ። እነዚህ ማዕከላት ከቤት ማስወጣት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለመፍታት ሊያግዙ ይችላሉ። ዝርዝር፦ resolutionwa.org/locations

  • የሕግ አማካሪ የማግኘ መብት። የሕዝብ እርዳታን የሚቀበሉ ወይም በጣም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ተከራዮች — ለአንድ ግለሰብ ዓመታዊ ገቢው $25,760 ወይም ለአራት ቤተሰብ $53,000 ከሆነ — ከቤት የማስወጣት የፍርድ ሂደት አገልግሎት ከጠበቃ በነጻ ማግኘት ይችላሉ። ከቤት የማስወጣት መከላከያ ማጣሪያ በ 855-657-8387 የስልክ መስመር ይደውሉ ወይም ኦን ላይን ያመልክቱ፦ nwjustice.org/apply-online

የበለጠ ለማወቅ ከመንግስት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ይማሩ

Office of the Attorney General (የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ) ጽሕፈት ቤት ስለነእነዚህ ፕሮግራሞች እና ሌሎች የአከራይ-ተከራይ ጉዳዮችን በተመለከተ በብዙ ቋንቋዎች ተጨማሪ የሕግ እና የፖሊሲ መረጃ በመስጠት ላይ ይገኛል፦ atg.wa.gov/landlord-tenant.

ስለ ሌሎች ወጭዎች እርዳታ መረጃ ለማግኘት 2-1-1 ላይ ይደውሉ

እንደ የማብራት ክፍያዎች ፣ የምግብ ፣ የብሮድባንድ እና ሌሎችም ላሉት ነገሮች እንዲከፍሉ ለመርዳት መረጃ መስጠት ከሚችል ሰው ጋር ለመነጋገርwa211.orgን ይጎብኙ ወይም ለ 2-1-1 ይደውሉ።

Last Updated 2021-10