ኣማርኛ
የቤት ውስጥ ፍጆታዎን ለመክፈል እገዛ ይፈልጋሉ?
በ COVID-19 ወረርሽን ወቅት የኤሌክትሪክ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ወይም የመጠጥ ዉሃ የፍጆታ ወጪዎችን መክፈል ካልቻሉ ፣ እገዛ ይገኛል።
ለፍጆታ ድርጂትዎ ይደውሉ። እነዚህን ሁለት ጥያቄዎች ይጠይቁ፦
- ለየትኞቹ የድጋፍ ፕሮግራም ብቁ ይሆናሉ?
- የባለፈው ቀሪ ሂሳብዎ ላይ የክፍያ እቅድ ማውጣት ይችላሉ?
የኤሌክትሪክ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ወይም የዉሃ መገልገያዎችን ለማግኘት እገዛ ይፈልጋሉ? በዚህ ገጽ ላይ በሚገኛው ካርታ ውስጥ አድራሻዎን ያስገቡ፦ https://www.commerce.wa.gov/utility-assistance/.
የቤት ውስጥ መገልገያ ክፍያዎችን በመክፍል ሰዎችን ለሚያገዘው የፌዴራል ፕሮግራም ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።
በገቢዎ ላያ በመመስረት፤ “LIHEAP” (ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰብ የሚሰጥ የቤት ውስጥ ሃይል ድጋፍ ፕሮግራም) ለሚባል የፌዴራል ፕሮግራም ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ለዉሃ ክፍያዎች አዲስ፣ ተመሳሳይ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። እነዚህ ብቁ ለሆኑ የገቢ ደረጃዎች ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው፦
- የቤተሰብ ብዛት 1 ለሆነ = የገቢ መጠን በወር ከ $1,595 በታች ወይም በዓመት ከ $19,140 በታች ለሆነ
- የቤተሰብ ብዛት 2 ለሆነ = የገቢ መጠን በወር ከ $2,155 በታች ወይም በዓመት ከ $26,860 በታች ለሆነ
- የቤተሰብ ብዛት 4 ለሆነ = የገቢ መጠን በወር ከ $3,275 በታች ወይም በዓመት ከ $39,300 በታች ለሆነ
ለመረጃ, ወደ 2-1-1 ይደውሉ ወይም በሚኖሩበት አከባቢ ለ “ለማህበረሰብ ድርጊት ወኪል” ይደውሉ። የእውቂያ መረጃን ለማግኘት ይህንን ካርታ ይጠቀሙ፦ https://fortress.wa.gov/com/liheappublic/Map.aspx
በሌሎች ወጪዎች ላይ ለማገዝ ሃብቶች ይኖራሉ። ለመረጃ ወደ 2-1-1 ይደውሉ።
ወረርሽኙ በዋሽንግተን ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ባልተጠበቁ ክፍያዎች ውስጥ ዘፍቋቸዋል። ብቻዎትን አይደሉም። ለሰዎች እንደ የቤት ኪራይ ፣ ምግብ ፣ ብሮድባንድ እና የመሳሰሉ ሌሎች ወጪዎችን በመክፍል የሚያግዙ ፕሮግራሞችን ሊያገናኝዎ ከሚችል ሰው ጋር ለመነጋገር 2-1-1 ላይ ይደውሉ።
Last Updated 2021-06
- ኣማርኛ (AM)
- العربية (AR)
- Chuuk (CHK)
- Duetch (DE)
- Español (ES)
- فارسی (FA)
- Français (FR)
- हिन्दी (HI)
- Lus Hmoob (HM)
- 日本語 (JP)
- ကညီ ကျိာ် (KAR)
- ខ្មែរ (KM)
- 한국어 (KO)
- ພາສາລາວ (LAO)
- Kajin Majōl (MH)
- Tu’un Savi (MX)
- မြန်မာစာ (MY)
- नेपाली (NE)
- Afaan Oromoo (OM)
- ਪੰਜਾਬੀ (PA)
- Português (PT)
- Limba română (RO)
- русский язык (RU)
- Gagana Samoa (SM)
- Af-Soomaali (SO)
- Kiswahili (SW)
- தமிழ் (TA)
- తెలుగు (TE)
- ภาษาไทย (TH)
- ትግርኛ (TI)
- Tagalog (TL)
- українська мова (UK)
- ارُدُو (UR)
- Tiếng Việt (VI)
- 简体中文 (ZHS)
- 繁體中文 (ZHT)